መተዳደሪያ ደንብ (styrdokument)
ደንብና ህግጋት ለመዋለ ህጻናትና ት/ቤቶች
የስዊድን መዋለ ህጻናትና ት/ቤቶች የሚመሩት በሚከተሉት ደንብና ህግጋቶች ነው።
የትምህርት ደንብ እና መመሪያው ለሁሉንም ደረጃዎች እና ት/ቤቶች ያካትታል። በተጨማሪም የጊዜ እና የስልጠና እቅድም አለው።
ይህ የትምህርት ደንብ እና መመሪያ ወሰን እና ገደብ ያለው ሆኖ ኮምዩኖች እና ት/ቤቶች ባላቸው መብት እንዲሁም ባላቸው ህግና ደንብ ውስጥ አካተው እና አስማምተው እንዲጠቀሙበት የተዘጋጀ ነው። በተጨማሪ ለማወቅ ስለ ansvarsfödelningen ማንበብ ትችላላችሁ።
ብሔራዊ ደንቦቹም
ሀ. በፓርላማ የተወሰነው የትምህርቱ ደንብ መሰረታዊ የሆኑ የት/ቤት ህጎችን ለሁሉም ት/ቤቶች ያካተተ ነው። ሀግና ደንቡ ጠለቅ ያለ መመሪያን ያካተተ እና ት/ቤቶች በተወሰነ ግብ እና አላማ ይዘው እንዲሰሩ የሚመራ ነው። በተጨማሪ ለማወቅ ስለ nationella styrdokumenten ማንበብ ትችላላችሁ።
ለ. ለሁሉም ት/ቤቶች ደንብ የተደነገጉ ማሟያ ስምምነቶች አሉ። በተለይም የአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች የትውልድ ቋንቋ የትምህርት አሰጣጥ ህግና ደንብ የያዘ ነው። ይህም በ Grundskoleförordningen ከምዕራፍ 2-3. 5.7. እና 9-14 ይገኛል። በ Gymnasieförordningen ምዕራፍ 5-6 እና ከ7-13 ይገኛል። የበለጠ ለማወቅ ስለGrundskoleförordning እና Gymnasieförordning ያንብቡ።
ሐ. የት/ቤቶች የስራ ደንብ (ካሪኩለም) የሚወሰነው በመንግስት ነው። በመዋለ ህጻናትና በት/ቤቶች የሚሰሩ ሁሉ ካሪኩለሙን የመከተል ግዴታ አለባቸው። የት/ቤቱን ሥራ እና የሚሰጠው የትምህርት ይዘት የሚወስነው ካሪኩለሙ ነው። ካሪኩለሙ ሁልጊዜ ወቅታዊ መሆን አለበት። ለከፍተኛ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና ለሁሉም የትምህርት ዘርፎች ግብ ያለው አገር አቀፍ እቅድ መንግሥት ያፀድቃል። የበለጠ ለማወቅ läroplanerna för förskolan, för grundskola inklusive förskoleklass och fritidshem och för gymnasiet ያንብቡ።
መ. መንግሥት በትምህርት ቤት የሚሰራበትን የመማሪያ እቅድ ይወስናል። እያንዳንዱ የትምህርት ዘርፍ የኮርስ ዕቅድ ፕሮግራሙን ፣ አላማውን እና አመሰራረቱን ይገልፃል። በተጨማሪም ተማሪው በኮርሱ መጨረሻ ማወቅ እና መድረስ የሚገባውን ደረጃ በግልጽ ያስቀምጣል።የበለጠ ለማወቅ ስለKursplaner och bedömningskriterier för modersmålsundervisning i grundskolan እና ስለ gymnasiet ያንብቡ።
ሠ. በይበልጥ ከትምህርት ሚኒስቴር ስለ አጠቃላይ ምክር (allmänna råd) ያንብቡ።
የማህረሰቡ(kommunens) የሥራ ሃላፊነት
የማህበረሰቡ(kommunens) የፖለቲካ ሃላፊዎች ስለ መዋለ ህፃናት እና ስለ ት/ቤቶች ትልቅ ሀላፊነት አለባቸው።
ሀ. እነዚህ የማህበረሰቡ(kommunens) ሃላፊዎች ስለ ት/ቤቶቹ ስራ መሟላት እና መሰራቱን የሚገልፅ የአጭርም ሆነ የረጅም እቅድ ማሳየት አለባቸው።
ለ. መዋለ ህፃናትና ት/ቤቶች የኮርስ እቅዳቸውንና ፕላናቸውን ሊያሳድጉ እንዲሁም ሊለውጡ ያቀዱትን በኮርሱ እቅድ ላይ መፃፍ አለባቸው። ት/ቤቱም ውስጣዊ የሆነ የጊዜ እቅድ መፃፍ አለበት። አንድ ወጥ የሆነ እቅድ እንዲወጣና እቅዱም ተግባራዊ እንዲሆን ግምገማ እንዲደረግበት መሻሻል ያለበትም እንዲሻሻል ተግባራዊነቱን የመከታተሉትና ሀላፊነት ያለባቸወ የየትምህርትቤቶቹ ዳይሬክተሮች ናቸው።
በተጨማሪም የትምህርት ሚኒስቴርን ፅሁፍ "Undervisning för elever med utländsk bakgrund och för nationella minoriteter" ያንብቡ።



