Till Tema modersmål

Tema modersmål - amhariska

amhariska

ኢትዮጵያ

Skriv ut

ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በሰሜን ምስራቅ የአፍሪካ ቀንድ በመባል በሚታወቀው አካባቢ የምትገኝ ከአፍሪካ በቆዳ ስፋቷ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ የያዘች አገር ናት፡፡ የምትገኘውም ከ30 _ 150 በሰሜን የምድር ወገብና ከ330 - 480 በምስራቅ ዋልታ ክልል ውስጥ ነው፡፡ አምስት አዋሳኝ አገሮች ሲኖሯት በምስራቅ በኩል ጅቡቲና ሶማሊያ፤ በሰሜንና በሰሜን ምስራቅ ኤርትራ፤ በደቡብ ኬንያ እና በምእራብ ሱዳን ናቸው፡፡ ጠቅላላ የቆዳ ሰፋት 1.14 ሚሊዬን ካሬ ኪሎ ሜትር ሲሆን በውስጧ 7000 ኪ.ሜ የሚደርስ ርዝማኔ ያላቸው አስር ትላልቅ ወንዞችና ወደ 7000 ካሬ ጠቅላላ ስፋት ያላቸው ሀይቆች አሏት፡፡

የህዝብ ብዛት

የህዝቧ ብዛት በ2007\2008 እ.ኤ.አ 78.2 ሚሊዮን ነው።

  • የሴት ቁጥር 38.7 ሚሊዮን (49.5%)ነው።
  • የወንድ ቁጥር 39.5 ሚሊዮን (50.5%) ነው።
  • በገጠር የሚኖረው ነዋሪ ቁጥር 83.9% ነው።
  • በከተማ የሚኖረው ነዋሪ ቁጥር 16.1% ነው።
  • የህዝብ ብዛት በ2.6% በየዓመቱ ያድጋል።
  • የህዝብ ብዛት በአንድ ካሬ ኪሎ ሜትር 68 ነው።

አማካኝ ዕድሜ

  • የሴቶች አማካኝ እድሜ 53.42 ዓመት ሲሆን
  • የወንዶች አማካኝ እድሜ 55.42 ዓመት ነው።

ቋንቋ

አራት መሰረታዊ የቋንቋ ቤተሰቦች ሲኖር እነርሱም ኩሺቲክ (Cushitic) ፣ ሴሜቲክ (Sematic) ፣ ኦሜቲክ (Omotic) ፣ ኒሎ ሻሮን (Nilo-Saharan) በመባል ይታወቃሉ።

በግምት 83 የተለያዩ ቋንቋዎችና ከ200 የሚበልጡ የአነጋገር ዘዬዎች በአገሪቱ ይነገራሉ።

አማርኛ የብሄራዊ ቋንቋ ሲሆን የንግድና የስራ መግባብያ ቋንቋዎች አማርኛ እና እንግሊዝኛ ናቸው።

ሀይማኖት

ክርስትና እና እስልምና

ምርጫ

የፌደራል ምርጫ በየአምስት ዓመቱ አንድ ጊዜ ይካሄዳል።

መልክአ ምድር

ኢትዮጵያ በውስጧ የተለያዩ መልክአ ምድር ያላት አገር ከመሆኗ በተጨማሪ የአየር ንብረት አፈር የእንስሳትና የዕፅዋት ስብጥር የሚስተዋልባት አገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ በጣም ከፍተኛ የሆኑ ተራሮች ከላያቸው ጠፍጣፋ የሆኑ አምባ የሚባሉ ኘላቶዎች ስምጥ የሆኑ ሸለቆዎች፤ ጥልቅ የወንዝ ሸለቆዎችና ሰፋፊ ሜዳዎች በውስጧ ይዛለች፡፡ ከባህር ጠለል በላይ 4620 ሜትር ከሚደርሰው ዳሽን ተራራ እስከ 148 ሜትር ከባህር ጠለል በታች እስከሆነው የዳሎል ዲኘረሽን ድረስ የሚሆን ልዩነት ያለው የከፍታና ዝቅታን የምታስተናግድ አገር ናት፡፡

ለም ከሆኑ መሬቶችና ተራሮች ምንም የማይታይባቸው ከሚመስሉ መሬቶች አንስቶ፣ ኢትዮጵያ በብዙ ገባሮችና ትላልቅ እንደ አባይ ተከዜ አዋሽ ኦሞ ዋቢ ሸበሌና ባሮ-አካቦ በመሳሰሉ ወንዞች የታደለች አገር ናት፡፡

ከሜዲትራንያን ምስራቃዊ መጨረሻ ተነስቶ፣ ደቡብ ምስራቅ አፍሪካ የምትገኘው ሞዛንቢክ ድረስ የሚደርሰው ታላቁ የስምጥ ሸለቆ ኢትዮጵያን ለሁለት ከፍሏት ያልፋል፡፡

የአየር ንብረት

ኢትዮጵያ እንደ መልክአ ምድራዊ አቀማመጧ የአየር ንብረቷም በተለያዩ ቦታዎች የተለያየ ሁኔታ ይታዩባታል፡፡ የመካከለኛው ኘላቶ አካባቢ ብዙም የማይፈራረቅ አይነት ወይናደጋማ አይነት የአየር ንብረት ይታይበታል፡፡ ዝቅተኛው የአየር ንብረት በአማካኝ 60c ሲሆን ነገር ግን ወደ ቀይባህር በረሀ አካባቢ 600c የሚደርስበት ጊዜዎች አሉ፡፡ በብዙ የአገሪቱ አካባቢ በክረምት ወራት ይኸውም ሰኔ ሀምሌና ነሀሴ ውስጥ ከፍተኛ የዝናብ መጠን ይመዘገባል፡፡ 

በከፍታና በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ የተነሣ በኢትዮጵያ ውስጥ ሦስት ዐይነት የአየር-ንብረት ክልሎች ይገኛሉ። እነሱም:-

  • ደጋ - ከፍታቸው ከባሕር ጠለል 2400 ሜትር የሚጀምር እና የሙቀት መጠናቸው ከ 16 ዲግረ ሴ.ግ የማይበልጥ፤
  • ወይናደጋ - ከፍታቸው ከባሕር ጠለል ከ1500 እስከ 2400 ሜትር፣ ሙቀታቸውም ከ16 ዲግረ ሴ.ግ እስከ 30 ዲግረ ሴ.ግ የሚደርስና፣
  • ቆላ - ከባህር ጠለል በታች ጀምሮ እስከ 1500 ሜትር ከፍታ ያላቸው፣ የሙቀት መጠናቸውም ከ30 ዲግረ ሴ.ግ እስከ 50 ዲግረ ሴ.ግ የሚደርስ አከባቢዎች ናቸው።

ዋናው የዝናብ ወቅት ከሰኔ አጋማሽ እስከ መስከረም አጋማሽ ሲሆን፣ ከሱ ቀደም ብሎ አልፎ አልፎ የሚጥል የበልግ ዝናብ በየካቲት እና በመጋቢት ይከሰታል። የተቀሩት ወራት በአብዛኛው ደረቅ ናቸው።

 

ሰዓት

GmT +3

የኢንተርኔት ዶሜይን        

.et

ስልክ ኮድ የኢትዮጵያ

 +251

አመታዊ አቆጣጠር መስከረም አንድ እስከ ነሐሴ 30 ሲሆን

ምንዛሪ

ብር ሲባል

አንድ ብር መቶ ሳንቲሞች አሉት። ቅጠል ብሮች ባለ 1፣ 5፣ 10፣ 50፣ 100 ናቸው።