Till Tema modersmål

Tema modersmål - amhariska

amhariska

የዱር እንሰሳትና አእዋፎች

የስዌን ቆርኪ

Skriv ut

የስዌን ቆርኪ

Swen_korki_1ብርቅየው የሰዌን ቆርኪ በኢትዮጵያ ብቻ ከሚገኙት ሰባት ጡት አጥቢ እንሰሳት አንዱ ነው። ቆርኪ ከትከሻው ከፍ ብሎ ከቂጡ ዝቅ ያለ ሲሆን ከአፉም ሾጣጣ ነው። የሰዌን ቆርኪ ከሌሎቹ አገሮች ቆርኪዎች የሚለየው በቀለሙ ነው። ቀለሙም ቸኮሌታማ ሲሆን ከበስተኋላው ነፃ ያለ ነው። ይህ እንሰሳ በአማካኝ የወንዱ ክብደት 150 እስከ 180 ኪሎ ግራም ይደርሳል። ሴቷ ቆርኪ ከወንዱ በመጠን ታንሳለች።

Läs mer...
 

ኒያላ

Skriv ut

 ኒያላ

ባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ቀይ ቀበሮና ኒያላን ጨምሮ በርካታ ብርቅዬ የዱር አነስሳትና አእዋፎች ይኖራሉ።

ኒያላ ብዙ ጊዜ የሚንቀሳቀሰው ሲመሻሽና ሲነጋጋ ነው። የሚመገበውም እንቡጦች፣ፍራፍሬዎች እንዲሁም ቅጠላቅጠሎችን ሲሆን ወንዱ ኒያላ የሚኖረው ብቻውን ወይም ተደባልቆ በቡድን ከ40 እስከ 50 በመሆን ነው።

ሴቷ ኒያላ እስክ 8 ወር አርግዛ ብዙ ጊዜ ይምትወልደው አንድ ጥጃ ብቻ ነው። ኒያላን የሚያጠቁ ብዙ እንሰሳት ሲኖሩ ከነዚህም ውስጥ አንበሳና አቦሸማኔ ይገኛሉ በዚህም ላይ በሰው ለስጋው ይታደናል። ኒያላ እስከ 16 ዓመት ያህል ሲኖር በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ ብርቅዪ እንሰሳ ነው።

Nyala