Till Tema modersmål

Tema modersmål - amhariska

amhariska

የቡሔ በአል አከባበር

Skriv ut

ቡሔ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የሚከበር በዓል ነው።

Buhie2የቡሔ በአል አከባበር በኢትዮጵያ ውስጥ ባህላዊም ሐይማኖታዊም ነው። በባህላዊ ስሙ ቡሄ ሲባል በሐይማኖታዊ ደግሞ ደብረታቦር በመባል ይታወቃል።

እየሱስክርስቶስ ያቆብን፣ ጴጥሮስን እና ዮሐንስን በመያዝ ወደረጅሙ ታቦር ወደ ተባለው ተራራ ይወጣል። ከዚያም መለኮ ተበብርሐን ተገጸ በፊታቸውም የእየሱስክርስቶስ ፊት እንደ ብርሐን በራ ልብሱም እንደብርሐን ነጭ ሆነ እንዲሁም ኤሊያስ እና ሙሴ ከእሱ ጋር ሲነጋገሩ ታያቸው። ጴጥሮስም እንዲህ አለ ጌታ ሆይ ብትወድ ለኛ በዚህ መሆንህ መልካም ነው ሶስት ዳስ በዚህ እንሥራ አንዱን ላንተ አንዱን ለሙሴ አንዱን ለኤልያስ አለው ይህን ሲናገር ደመና ጋረዳቸው በደመናው ውስጥም ድምጽ ተሰማ

የምወደው እና ደስ የምሰኝበት ልጄ እሱ እየሱስ ነው እሱንም ስሙት አላቸው።

የቡሔ አመጣጥም የእውቀት አባቶች እንደሚናገሩት በደብረታቦር ተራራ ላይ የተደረገውን ተአምር ምክንያት በማድረግ ነው። በቡሔ እለት ችቦ የሚበራበት ምክንያት በዛን እለት የታየውን ተአምረብርሐን ለማስታወስ ሲሆን ጅራፍ የሚጮህበት ደግሞ በእለቱ የነበረውን ነጎድጓዳዊ ድምጽን ለማስታወስ ነው። እንዲሁም ሙልሙል ዳቦ ለሚጨፍሩት ልጆች የሚሰጥበት ዋናው ምክንያት በብርሐኑ ምክንያት ቀኑ በመርዘሙ እረኞች በመታለል በታቦር ተራራ ስር ሆነው እየጨፈሩ ቀንና ሌሉትን መለየት ስለተሳ ናቸው ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን በመዘንጋታቸው ያሳሰባቸው እናቶች ለልጆቻችን ተራቡ በማለት ሙልሙል በመያዝ መሄዳቸውን ምክንያት በማድረግ ነው።

የዚህ በአል አከባበር ከዚህ ከእየሱስክርስቶ ታሪክ ጋር ተያይዞ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ነው።

በቡሔ ቀን ልጆች ሆያሆዬ! ማለት የሚጨፍሩት በዛን ቀን በደብረታቦር ተራራ ስር እረኞች ሲጫወቱ የነበረውን ምክንያት በማድረግ ነው።

ሆያሆዬ! ማለት "ሆይ" የሚለውን ቃል ደጋግመህ በል ማለት ነው።

"ቡሔ" ማለት መገለጥን (መላጣ) ማለት ነው።

ሐይማኖታው ምክንያቱም ግርማ መለኮት የተገለጠበት ማለት ሲሆን ባህላው ትርጉሙ

ደግሞ ክረምት አልፎ በጋው የሚመጣበት ወቅት በመሆኑ ነው።

በየተለያዩ ያአገሪቱ ክፍል በቡሔ ቀን ልጆች በቡድን በቡድን በመሆን ሆያ ሆዬ እያሉ በመጨፈር በአሉን ያከብሩታል።

ሆያ ሆዬ በዚህ መልኩ ይጨፈራል።

ወደ ጭፈራ በመንገድ ሲሄዱ እንዲ በማለት ይጨፍራሉ።

ሆያ ሆዬ

አስዮ ቤሌማ ኦሆሆ

አሃ በል

ቤሌማ ማለቴ

አወይ ልጅነቴ

አስዮ ቤሌማ ኦሆሆ

በደረሱበት ቤት በር እንዲከፈትላቸው እንዲ በማለት ይጨፍራሉ።

መጣና መጣና

ደጁን ልንጠና

ክፈቱልን በሩን

የጋሼ (............. )

በግቢው ከገቡ ኋላ እንዲ በማለት ይጨፍራሉ።

እዛማዶ ጭስ ይጨሳል

አጋፋሪ ይደግሳል

ያንን ድግስ ውጬ ውጬ

በድንክ አልጋ ተገልብጬ

ያችም ድንክ አልጋ አመለኛ

ያለ አንድ ሰው አታስተኛ

 ሆይሽ ሆዬ ሎሚታ

ልምጣ ወይ ወደማታ *2*

የቤቱን ባለቤት ሲያመሰግኑ እንዲ በማለት ይጨፍራሉ።

የእኔ እመቤት የፈተለችው

እንኳን ሰውና ማርያም ሰራችው

ለዛች ለማርያም እዘኑላት

አመት ተመንፈቅ አለቀላት

ሆይሽ ሆዬ ሎሚታ

ልምጣ ወይ ወደማታ *2*

የቡሄ ሙልሙል ከተሰጣቸው በኋል እንዲ በማለት ይጨፍራሉ።

ክበር በስንዴ ክበር በጤፍ

ምቀኛህ ይርገፍ * 3 *

እምዬን አደራ

አንቺ አሞራ

ጨርሰው ሲወጡ እንዲ በማለት እጨፈሩ ይሄዳሉ።

እርግብ ስትቀመጥ

ዳቦህን ግመጥ

እርግብ ስትነሳ

ዳቦህን አንሳ

በተለያዩ ቦታዎች በአብዛኛው በተመሳሰለ መልኩ ይከበራል

                                                                                                                        ሆያ ሆዬን ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ  

AV Tegegne Yirdaw          በተገኝ ይርዳው