ስለ ትውልድ ቋንቋ
የአማርኛ ትምህርት አስጣጥና በዙርያው ያሉ ህግጋት
የአማርኛ ቋንቋ በስዊድን ት/ቤቶች
የአማርኛ ቋንቋን ለመማር ህግና ደንቡ የሚያዘው አንድ ተማሪ ከወላጆቹ አንዱ ወይም ሁለቱም የትውልድ ቋንቋቸው ስዊድንኛ ያልሆነ ከሆነና ተማሪው ፍላጎት ሲኖረው። በሌሎች የትምህርት አይነቶች የተለየ እገዛ (ጽቱዲአሃንድለድኒንግ)ተማሪው በሌሎች የትምህርት አይነቶች የተለየ የትምህርት አገዛ የሚያገኘው ማግኘት የሚገባው ሆኖ ሲገኝ ነው።
አላማው ጥረቱና እቅዱ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤት
ተማሪው በትውልድ ቋንቋው መናገርና መጻፍ አንዲችል።
የተለያዩ ጽሁፎችን በማንበብ የቋንቋ ችሎታውን ማዳበር አንዲችል።
የትውልድ ቋንቋውን አገነባብ በመረዳትና ከስዊድን ቋንቋ ጋር በማወዳደር የሁለቱም ቋንቋዎች ተናጋሪነቱን ማዳበር።
ስለትውልድ አገሩ ታሪክ ፣ ባሀልና የማሀበራዊ ኑሮ ይዞታ በማወቅ በስዊድን ካለው ይዞታ ጋር ማወዳደር።
ማንነቱን ማወቅና በራስ የመተማመን ስሜትን በማዳበር የሁለት የተለያዩ የባህል ክፍሎች አካል መሆን።
የማንበብ ልምድን መስረት መጣልና የተለያዩ ጽሁፎችን ማንበብ በተጨማሪም ጽሁፎችን ለሌላ አገልግሎት ማዋል።
የታሪክ ቅርሶችን በማጥናትና በማወቅ ከራስ ጋር ያለውን ዝምድና ማስተያየት።
የትውልድ ቋንቋን በመልመድና በመገልገል በዛም ተጠቅሞ የቃላትንና የሌሎች አውቀቶች ችሎታን ማዳበር።
አላማው ጥረቱና እቅዱ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
የትምህርት ቤቱ አላማና ጥረት ተማሪው የትውልድ ቛንቛ ትምህርት ለምን እንደሚስጥ ግንዛቤ እንዲኖረውና በበለጠ ማንነቱንና ባህሉን እውቆና ተገንዝቦ ለዛም ባህል ስሜትና ፍላጎት እንዲያዳብር ማድረግ ነው።
ተማሪው ማንነቱን በማወቅና ስለባህሉና ስለራሱ ስሜት የመግለጽ ችሎታ አንዲኖረው በተጨማሪም
አናሳ ባሀሎች በዚህ በስዊድን አንዲያድጉ የማድረግ።
በትውልድ ቋንቋው ስሜቱንና ማንነቱን የመግለጽ ችሎታን ማዳበርና ለተለያዩ አላማዎች መጠቀም።
የትውልድ ቋንቋን እንደ አንድ እውቀትን የማዳበርያ መሳርያ በመጠቀም የቃላትን ፣የአባባልንና የአነጋገርን ችሎታ በተመረጠ የትምህርት ዘርፍ ማዳበር።
በትውልድ ቋንቋ አንብቦ መረዳትን በማሳደግ ተማሪው በቋንቋው መጽሀፍቶችን ፈልጎ በማንበብ እውቀቱን በማዳበር ደስታን እንዲያገኝበት ማነቃቃት።
ስለ ቋንቋው ታሪካዊ አመጣጥና እድገትን ማወቅ።
በዚህ በስዊድን በአናሳና ብዛት ተናጋሪ ባላቸው ቋንቋዎች መሃል ያለውን ልዩነት መገንዘብና ማወቅ።
በተለያዩ ጋዜጦች እንዲሁም መጽሄቶች የወጡ ስለተማሪው የትውልድ አገር የአኗኗር ዘዴንና ታሪክን አንዲሁም ባህልን በመፈለግና በማጥናተ እዚህ ካሉ ተመሳሳይ አናሳ ባህል ካላችው የህብረተስብ ክፍሎች ጋር በማወዳደር እራስን በማወቅ አካባቢን በበለጠ ማወቅና መረዳት።
የራስን አገር ባህል በመማርና በማወቅ ከራስ ሁኔታ ጋር ለማዛመድ መሞከር።