Till Tema modersmål

Tema modersmål - amhariska

amhariska

የሚያስደስተኝ ነገር

Skriv ut

የሚያስደስተኝ ነገር

እኔ በቤተሰቦቼ ደስ ይለኛል።

እነሱ በጣም ይጠቅመኛል።

በእነሱ ደስ ይለኛል።

በሚያስፈልገኝ ነገር ሁሉ ምንጊዜም ከእኔ ጋር ናቸው።

ቤተሰቦቼ ለእኔ እንደ ጓደኞቼም ናቸው።

እነሱ ጥሩ አርአያዎቼ ናቸው።

ሳዝን ያጥናኙኛል እንዲሁም ይረዱኛል።

ጎበዝ እንድሆን ያበረታቱኛል።

እንዳልበሳጭ ይመክሩኛል።

አንድ አንድ ጊዜ እንጣላለን ግን ቶሎ እንታረቃለን።

ክርስትያኖች ናቸው።

ስለ ክርስትና ያስተምሩኛል።

ትክክል ስለ ሆነ እና ትክክል ስላልሆኑ ነገር ያስረዱኛል።

እነሱ ባያስተምሩኝ ጥሩ ልጅ አልሆንም ነበር።

እሁድ እሁድ አብረን ቤተክርስትያን አብረን እንሄዳለን።

እኔ ወደ ቤተክርስትያን ስሄድ ትልቅ ደስታ ይሰማኛል።

ቤተክርስትያን እንደ ሁለተኛ ቤቴ ይሰማኛል።

ብዙ ዘመዶች አሉኝ።

ያሉኝ ዘመዶች በዮተቦሪ፣ በእንግሊዝ፣ በስዊዘርላንድ እንዲሁም በኢትዮጵያ ይኖራሉ።

በመጨረሻ ማለት የምፈለገው ቤተሰቦቼ ለህይወቴ ትልቅ ቦታ አላቸው።

ይህን የመሰለ ቤተሰብ ስለ ሰጠኝ አመሰግነዋለው።

ባስልኤል ብርሃን
2010/12/09