Till Tema modersmål

Tema modersmål - amhariska

amhariska
2010-04-19 22:00

ቋንቋ

Skriv ut

የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እና ጥበቃዉ

ቋንቋ የአንድ ህብረተሰብ ባህል እዉቀት እና ፍላጎት አጠቃሎ የያዘ፣ የአንድ ህብረተሰብ ምንነት መግለጫ ነዉ። ቋንቋ ሞተ ስንል ምን ማለታችን ነዉ? በአገራችን ስንት ቋንቋዎች ይነገራሉ? በሞት ላይ ያሉ አልያም የሞቱ ቋንቋዎችስ ስንት ናቸዉ?

የተባበሩት መንግስትታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ተቋም UNESCO በቦን ከተማ ያለዉ ቅርንጫፍ በአለማችን ዙርያ ሚነገሩ 6000 ያህል ቋንቋዎች መካከል ግማሹ እንዳይጠፋ ያሰጋል የሚል መግለጫ ከሁለት ሳምንት በፊት ማዉጣቱ የሚታወስ ነዉ። ይህንን ጥናት UNESCO ያወጣዉ የካቲት 14 ቀን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አመታዊዉን የእናት ቋንቋ ወይም የአፍመፍቻ ቀን ለመጠበቅ ሲባል የተወሰነዉን ቀን አስቦ የዋለ እለት ነበር። በአገራችን ኢትዮጵያ ስንት ቋንቋዎች ይነገራሉ? በሞት ላይ ያሉ አልያም የሞቱ ቋንቋዎችስ ስንት ናቸዉ? 

 
2011-05-28 08:31

የ2011 መምህራን አገር አቀፍ ስብሰባ

Skriv ut

የአመቱ አገር አቀፍ የአማርኛ መምህራን ስብሰባ በማርዬሀምን(Mariehamn) በ2011/05/16 በጥሩ ሁኔታ ተከናውኗል።

በስብሰባው ላይ ወደ 14 የሚሆኑ መምህራኖች ከመላው የስዊድን ክፍል የተገኙ ሲሆን በተለያዩ ነጥቦችም ላይ ተወያይተዋል።

Läs mer...
 
2010-11-12 20:16

ተረቶች

Skriv ut

እሣትና ውሃ

እሣትና ውሃ ተባብረው አንድ በሬ ገዙ። የዕለቱ ዕለት በሬያቸውን  ሌባ ሠረቀባቸው። በዚህ ጊዜ አቶ እሣት እንዲህ አለ።

" ባልንጀሬ ሆይ ያው እንደምታውቀው ካንተ በስተቀር ሁሉንም አሸንፋለሁ። ስለዚህ አሁን ባፋጣኝ ተነስቼ ቤቱንም፤ደኑንም፤ሣሩንም አቃጥዬ የበሬያችንን ሌባ ፈልጌ ላግኘው" አለው።

ውሃ በበኩሉ

"ወንድም ጋሼ እሣት ምነው እንደዚህ ማለትህ የሰረቀውንም ደህነኛውንም አንድ ላይ ማቃጠል አይገባም። ሌባውን ለመያዝ ከሆነ የሚቸግረን ነገር የለም። አሁን እናገኘዋለን" ብሎ አጽናናው።

"እንዴት አድድርገን " ቢለው

"እጠብስ ያለ ካንተ፤ አጥብ ያለ ከኔ ብቅ ይላል። በዚህ ጊዜ እንይዘዋለን" አለው:

ይህን ከታባባሉ ከጥቂት ጊዜ በሁዋላ አንዱ ቅልጥም ይዞ ወደ እሣት መጣ። አንደኛው ደግሞ ጨጉዋራ ሊያጥብ ወደውሃ ዘንድ ጎራ አለ። በዚህ ጊዜ ሌቦቹ ስለታወቁ ተይዘው ታሰሩ።

 
2010-10-31 20:10

ጠቃሚ ምክሮች

Skriv ut

"በትልቁ ተመኝ ሆኖም ባለህና በትንሹ ተደሰት"

"የሰዎችን ተስፋ አትውሰድ ምናልባት ያላቸው አንድ ተስፋ ያ ሊሆን ይችላልና"

"ባያስፈልግህ እንኳን ከሚገባህ በላይ ደግ ሁን"

"እንደ አንድ እንደምታውቀው ሰው ቅንና ደስተኛ ሁን"

"በተቻለህ መጠን እራስህን ለማሻሻል ጥረት አድርግ"

"ነገሮችን አታጋን"

"በጥምር ያለን ነገር አትበትን"

"የተዋስከውን ነገር ስትመልስ ከተረከብክበት በተሻለ ይዘት መልስ"

"ስኬትህን የምትለካው ባለህ ጤንነት፣መረጋጋት፣ፍቅር፣ደስታ ሊሆን ይገባል"

"አንድን ሰው መውደድህን የምትገልጽበትን አጋጣሚ በፍጹም አትለፍ"

 

በተገኝ ይርዳው

 
2011-02-26 22:37

ወንዞች በኢትዮጵያ

Skriv ut

ወንዞች በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከሚገኙት ዋና ዋና ወንዞች በጥቂቱ።

የአባይ ወንዝ          የተከዜ ወንዝ             የአዋሽ ወንዝ

የጊቤ ወንዝ         የዋቢሸበሌ ወንዝ      የገናሌ ወንዝ

የአባይ ወንዝ

Abay_61በአገራችን ካሉት ወንዞች በትልቅነቱም ሆነ በርዝመቱ የታወቀው አባይ የሚነሳው ከጣና ሐይቅ ሲሆን የሰሜኑን ምእራባዊ ክፍል በማቋረጥ 1450 ኪ.ሜ ተጉዞ ወደ ሱዳን ክልል ይገባል። በአጠቃላይ አባይ ከመነሻው እስከ መድረሻው 6670 ኪ.ሜ እርዝማኔ ሲኖረው የቆዳ ስፋቱም 2.9 ሚሊየን እስኩየር ኪ.ሜ ነው።

Läs mer...
 
2011-02-27 14:37

ላሊበላ

Skriv ut

የላሊበላ ቤተክርስትያን

Lalibela_1የላሊበላ ቤተጊዮርጊስ ቤተክርስትያን አሰራር በአለም ተደናቂነትን ያተረፈ እና የአሰራሩም ሁኔታ ለብዙዎች ግራ የሚያጋባ ነው። ንጉሥ ላሊበላ የውቅር አብያተክርስቲያናት በመባል የሚታወቁትን ከአንድ ወጥ ድንጋይ ተቦርቡረው እና ተፈልፍለው 11 ቤተክርስቲያናት እንዲሰሩ አድርጓል።

Läs mer...
 
  • «
  •  Första 
  •  Föregående 
  •  1 
  •  2 
  •  3 
  •  4 
  •  5 
  •  6 
  •  7 
  •  Nästa 
  •  Sista 
  • »
Sida 1 av 7