የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እና ጥበቃዉ
ቋንቋ የአንድ ህብረተሰብ ባህል እዉቀት እና ፍላጎት አጠቃሎ የያዘ፣ የአንድ ህብረተሰብ ምንነት መግለጫ ነዉ። ቋንቋ ሞተ ስንል ምን ማለታችን ነዉ? በአገራችን ስንት ቋንቋዎች ይነገራሉ? በሞት ላይ ያሉ አልያም የሞቱ ቋንቋዎችስ ስንት ናቸዉ?
የተባበሩት መንግስትታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ተቋም UNESCO በቦን ከተማ ያለዉ ቅርንጫፍ በአለማችን ዙርያ ሚነገሩ 6000 ያህል ቋንቋዎች መካከል ግማሹ እንዳይጠፋ ያሰጋል የሚል መግለጫ ከሁለት ሳምንት በፊት ማዉጣቱ የሚታወስ ነዉ። ይህንን ጥናት UNESCO ያወጣዉ የካቲት 14 ቀን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አመታዊዉን የእናት ቋንቋ ወይም የአፍመፍቻ ቀን ለመጠበቅ ሲባል የተወሰነዉን ቀን አስቦ የዋለ እለት ነበር። በአገራችን ኢትዮጵያ ስንት ቋንቋዎች ይነገራሉ? በሞት ላይ ያሉ አልያም የሞቱ ቋንቋዎችስ ስንት ናቸዉ?


mhariska (



